ከኮሪያ የመጡ የክህምና ባለሙያዎች ከኮሪያ ሆስፒታል ጋር በመሆን በዱከም ከተማ ነፃ የህክምና እየሰጡ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኮሪያ የመጡ የህክምና ባለሙያዎች ከኮሪያ ሆስፒታል ጋር በመጋራ በመሆን በዱከም ከተማ ነፃ የክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
የህክምና ባለሙያዎቹ ከዱከም ከተማ ጤና ጣቢያ ጋር በመተባበር ነው ለሶስት ቀናት የሚቆየውን ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት የጀመሩት።
በነፃ የህክምና አገልግሎቱ የሰው ሰራሽ ጥርስ ተከላ፣ የውስጥ ደዌ፣ ፊዚዮቴራ እና የነርቭ ህክምና ነው እየተሰጠ ያለው።
የነፃ የህክምና አገልግሎቱን በዱከም ከተማ በኮሪያ ባለሀብቶች የተገነባው ኢኮስ የብረታብረት ፋብሪካ መሆኑም ተገልጿል።
የዱከም ጤና ጣቢያ ሃላፊ አቶ ታምራት ማሞ እንደለገጹት፥ በ22 የህክምና ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከ1 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢኮስ ብረታብረት ፋብሪካ የነፃ ህክምና አገልግሎት አስተባባሪ
ቦ ውንክ ኪን፥ ፋብሪካው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር አብሮ የመስራት እና የማደግ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ
ይህንን የማህበረሰብ አገልግሎት ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
አገልግሎቱ በቀጣይም በተለያዩ ጊዜያት ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉ ሲሆን፥ ከዱከም ከተማ በተጨማሪም በጅማ፣ በሀረር፣ በዲላ እና በድሬ ደዋ ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
@FBC
No comments:
Post a Comment