Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ
Monday, 2 September 2019
ዳቦ ቤቶች በህገወጥ መንገድ መሸጥ መድረሳቸው
ዳቦ ቤቶች የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በህገወጥ መንገድ እስከ መሸጥ መድረሳቸው ተነገረ በመድረኩ ለውይይት በወቀረበው ሰነድ ላይ እንደተገለፀው መንግስት ለህዝብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ሲል የአንድ ዳቦ ዋጋ በ1 ብር 30 ሳንቲም ተምኖ ለዚህ የሚውል ስንዴን በድጎማ በ550 ብር እያቀረበ ይገኛል፡፡
ሆኖም ዳቦ ቤቶች ስንዴውን ገበያ በማውጣትና ‘ልዩ ስንዴ’ በማለት በ2 ሺህ ብር እየሸጡ 1 ብር 30 ሳንቲም የነበረ የዳቦ ዋጋ 3 ብር ድረስ ሲሸጥ እንደተደረሰበት በሰነዱ ላይ ቀርቧል፡፡
ከዚህ ባለፈ ዳቦ ቤቶች የተፈቀደላቸው ዳቦ እንዲያቀርቡ ቢሆንም ኩኪስ፣ዶናት፣ ኬክና መሰል ምርቶችን በድጎማው ስንዴ አምርተው በመሸጥ ላይ እንደሚገኙም በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረት ቁጥጥር ሲደረግ በተቀመጠላቸው ዋጋ መሰረት ሲሰሩ የነበሩ ዳቦ ቤቶች አርበኞች፤ ሮዛ፤አፍሪካ እና ምስራቅ ዳቦ ቤቶች ብቻ መሆናቸውም ተያይዞ ተገልጿል፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Biruh Media
በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና
Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...
No comments:
Post a Comment