Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Tuesday 10 September 2019

ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ ውዝግብ አስነሳ


በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ነው፡፡
ባለቤትነቱ የአቶ ደነቀ ሸለመ የሆነው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ ገዢዎችን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የወይዘሮ ሃጫልቱ በድሩን 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ላይ አነጣጥሮ ከጆሮዋ ላይ በጥሶ ይውጣል።

 ነገሩ ከተከሰተ በኋላ የዶሮው ባለቤትና የወርቋ ባለቤት ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባሉ፡፡

No photo description available.


የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው ወዲያው ታርዶ ወርቃቸው እንዲሰጣቸው ቢሹም የዶሮው ባለቤት ደግሞ በጉዳዩ አልተስማሙም።
ነገሩ መክረሩን ያዩት ገቢያተኞች ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ በማድረግ በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡


ጉዳዩ እንግዳ የሆነበት የወሊሶ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ጣቢያም ጉዳያቸውን በመስማማት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል።

የዶሮው ባላቤትም ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው የሚያወጣውን ዋጋ ከፍለው ዶሮውን ይረከቡኝ ሲሉ ይስማማሉ።


አቶ ደነቅም የወርቁ ባለቤት 250 ብር እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ባለ ወርቋ የተጠየቀውን ብር የለኝም በማለታቸው 150 ብር ሰጥተዋቸው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ነው የወሊሶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ

የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ከበደ በዳዳን ጠቅሶ ኢዜአ የዘገበው።
@ ኢዜአ

No comments:

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...