Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Monday, 16 September 2019

የ“ጊፋታ አዋርድ” ሽልማት ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሰጠ



የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ “ ጊፋታ አዋርድ” የተሰኘ የምስጋናና የዕዉቅና ሽልማት ተበረከቶላቸዋል::

በወላይታ ሶዶ “አርአያዎቻችን በረከቶቻችን ናቸው” በሚል መርህ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋናና ዕውቅና ስነ-ስርዓት ሲካሄድ

በስነ-ስርዓቱ ወቅት አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ በተለዩ አምስት ዘርፎች በሃገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጎ ተጽዕኖ የፈጠሩ 45 ግለሰቦች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል፡፡
በፖለቲካ፣ በንግድና ቢዚነስ፣ በኪነ-ጥበብ ፣በትምህርት ፣ባህልና ኃይማኖትና ህክምናው ዘርፎች ከአካባቢ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ በጎ አስተዋጽኦ የነበራቸው 45 ግለሰቦች ለመጀመሪያ ዙር እንዲታወሱና እንዲመሰገኑ ሽልማቱ እንደተሰጣቸው ተደርጓዋል፡፡

በኃይማኖቱ እነ አቡነ ተክለ-ኃይማኖትና አባባ ዋንዳሮን ጨምሮ በህይወት የሌሉ ነገር ግን አከባቢውን በበጎ መልኩ ያስተዋወቁ ሽልማቱና ዕውቅናዉ ከተበረከተላቸው መካከል ተጠቅሰዋል፡፡

በፖለቲካ አመራርና በትምህርት በሌሎች ጉዳዮች እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማበረከቱት አስተዋጽኦ ሽልማቱ የተበረከተላቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና ባለቤታቸዉ ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ናቸው፡፡

ለአቶ ኃይለማሪያ በአካባቢው ባህል መሰረት በፖለቲካው የአመራር ብስለትና ክህሎት በቀጣይም ከአብራኩ መሪ አይጥፋ በሚል የሚሰጥ ጦር፣ጋሻና የፈረስ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨረሲቲ እንዲመሰረት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በእጅ ጥልፍ የተሰራ ምስል ተሸልመዋል።

አቶ ኃይለማሪያም ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ የተዘጋጀው ስነስርዓት በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥና የአንድነት ጉዞ ለማጠናከር የጎላ አስተዋጽኦ አንደሚኖረዉ ተናግረዋል።

“ጊዜው የይቅርታ ነው” ያሉት አቶ ኃይለማሪያም በነበራቸው የስልጣን ቆይታ ወቅት የተፈጠሩ ስህተቶችን ህዝቡ ይቅር እንዲላቸው በመጠየቅ በቀጣይም ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ኢዜአ

No comments:

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...