Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Wednesday 11 December 2019

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ሊደረግ ነዉ

ለዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ  አህመድ የጀግና  አቀባበል ስነ ስርዓት ሊደረግ ነዉ ።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ ከኖርዌይ ኦስሎ ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ስነ-ስርዓት ይደረግላቸዋል ተብሏል። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የታክሲ ማህበራት ለአቀባበል ስነ ስርዓቱ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነም ታዉቋል ። የአቀባበል ስነ ስርዓቱም ከማለዳው  ጀምሮ  የሚካሄድ ሲሆን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ድረስ የጀግና እና የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡

Monday 2 December 2019

"በኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጉዞ

"በኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ እና የአሜሪካንን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ዛሬ ጠዋት ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ገብተዋል::" ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ከቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ  "በአጠቃላይ ከመነሻው ጀምሮ በመደመር ፍልስፍናም ሆነ በውህደቱ ጉዳይ ላይ እኔ ያመንኩበት እንዳልሆነ ለሥራ አስፈጻሚው በስፋት ገልጫለሁ።

 ውህደቱ ትክክል አይደለም፤ ትክክል ቢሆን እንኳ ጊዜው አይደለም ብዬ ስለማምን በግል አቋሜ ራሴን  አግልዬ ነው የቆየሁት። ይህ አይሆንም ያልኩት እኛ የኦሮሞ መሪዎች ሕዝቡ አምኖብን ትልልቅ ጥያቄዎችን ሰጥቶን እኛም እንመልሳለን ብለን ቃል ገብተናል። ይህን ጥያቄ እንመልሳለን ያልነው እንደ ኦዲፒ ነው እንጂ እንደአገር በተመሰረተው ፓርቲ አይደለም። የሕዝቡን ጥያቄ ሳንመልስ ይህን ማድረግ ትክክል አይደለም። ቃልኪዳናችንን መብላት ይሆናል።ሕዝቡ ጥያቄውን ቆጥሮ እንደሰጠን መመለስ አለብን።"
በማለት ከሬዲዮኑ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለመጠይቅ በመግለፃቸው መነጋገሪያ እንደነበሩ ይታወሳል ።

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...