Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ - በፋውንዴሽኑ የምስረታ ዝግጅት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። በልደታ አካባቢ ለፋውንዴሽኑ የሚሆን የመስሪያ ቤት ቦታም ተበርክቷል ።
ፋውንዴሽኑ ዶክተር አምባቸው በህይወት እያሉ የጀመሯቸውን ሊሰሯቸው የሚችሏቸውን ስራዎች ለማስቀጠል እንደሆነ የዶክተር አምባቸው ልጅ መዓዛ አስታውቃለች።
ፋውንዴሽኑ በትምህርት፣ በጤና እና በአረንጓዴ ልማት ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ እውነትንና ሀቀኝነትን ይዞ የአገርን ልማት የሚያግዝ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።
No comments:
Post a Comment