ደኢህዴን የሃዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሲዳማ እና የሃድያ ዞን ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ከሃላፊነት ማገዱን ይፋ አድርጓል። በሌላ በኩል ንቅናቄው ዛሬ በጀመረው ለ5 ቀናት ይዘልቃል በተባለው ስብሰባ በሃገራዊ እና ክልልላዊ ወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች እና በክልል ለመደራጀት በቀረቡ ጥያቄዎች መነሻነት የተዘጋጀው የጥናት ውጤት ላይ ይመክራልም ተብሏል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሲዳማ እና የሃድያ ዞን ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ከሃላፊነት ማገዱን ይፋ አድርጓል። በሌላ በኩል ንቅናቄው ከከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮቹ ጋር ዛሬ መምከር ጀምሯል።
ለ5 ቀናት ይዘልቃል የተባለው ይኽው ስብሰባ ከሚመክርባቸው ጉዳዮች መካከል ሃገራዊ እና ክልልላዊ ወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች እና በክልል ለመደራጀት በቀረቡ ጥያቄዎች መነሻነት የተዘጋጀው የጥናት ውጤት ይገኙበታል።
No comments:
Post a Comment