Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ
Saturday, 31 August 2019
Ethiopia : ስሜትን መግራት አነቃቂ ንግግር በዶክተር አደራ | Motivational Speech by Dr Adera Part 3
via https://youtu.be/0qQ4yYlacG4
ከኮሪያ የመጡ የክህምና ባለሙያዎች ነፃ ህክምና እየሰጡ ነው
ከኮሪያ የመጡ የክህምና ባለሙያዎች ከኮሪያ ሆስፒታል ጋር በመሆን በዱከም ከተማ ነፃ የህክምና እየሰጡ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኮሪያ የመጡ የህክምና ባለሙያዎች ከኮሪያ ሆስፒታል ጋር በመጋራ በመሆን በዱከም ከተማ ነፃ የክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
የህክምና ባለሙያዎቹ ከዱከም ከተማ ጤና ጣቢያ ጋር በመተባበር ነው ለሶስት ቀናት የሚቆየውን ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት የጀመሩት።
በነፃ የህክምና አገልግሎቱ የሰው ሰራሽ ጥርስ ተከላ፣ የውስጥ ደዌ፣ ፊዚዮቴራ እና የነርቭ ህክምና ነው እየተሰጠ ያለው።
የነፃ የህክምና አገልግሎቱን በዱከም ከተማ በኮሪያ ባለሀብቶች የተገነባው ኢኮስ የብረታብረት ፋብሪካ መሆኑም ተገልጿል።
የዱከም ጤና ጣቢያ ሃላፊ አቶ ታምራት ማሞ እንደለገጹት፥ በ22 የህክምና ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከ1 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢኮስ ብረታብረት ፋብሪካ የነፃ ህክምና አገልግሎት አስተባባሪ ቦ ውንክ ኪን፥ ፋብሪካው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር አብሮ የመስራት እና የማደግ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ይህንን የማህበረሰብ አገልግሎት ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
አገልግሎቱ በቀጣይም በተለያዩ ጊዜያት ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉ ሲሆን፥ ከዱከም ከተማ በተጨማሪም በጅማ፣ በሀረር፣ በዲላ እና በድሬ ደዋ ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
@FBC

Ethiopia : ስሜትን መግራት አነቃቂ ንግግር በዶክተር አደራ |Motivational Speech by Dr Adera Part 2
via https://youtu.be/mVcWTUNkeyg
Friday, 30 August 2019
Ethiopia : ስሜትን መግራት አነቃቂ ንግግር በዶክተር አደራ |Motivational Speech by Dr Adera Part 1
via https://youtu.be/fQu5BTl5WfU
Tuesday, 27 August 2019
የአ.አ. ፖሊስ ኮሚሽን ኅብረተሰቡን ይቅርታ ጠየቀ
Biruh Media - https://biruhmedia.blogspot.com
አዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ነሐሴ 20 ቀን 2011 ላይ ‘ሕጋዊ የኮሚሽን ሥራ እንሠራለን’በሚሉ እና ‘እኛም ሰፈራችን ስለሆነ እንሠራለን’ በሚሉ ግለሰቦች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ የፖሊስ አባላት የወሰዱት እርምጃ አነጋጋሪ ሆኗል።
በአካባቢው የነበሩት ፖሊሶች ፀብ ውስጥ የነበሩትን ግለሰቦች ‘ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዳችሁ ዳኝነት ታገኛላችሁ’ ቢሉም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አለመግባባት ተፈጥሮ የፖሊስ አባላቱ የተወሰኑ ሰዎችን መደብደባቸውን የአ.አ. ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽን እና የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለኢቲቪ አራት ማዕዘን ዝግጅት ክፍል አረጋግጠዋል።

ፖሊሶቹም ራሳቸው ደንብ ልብሳቸውን ለብሰው፣ ሥራ ላይ ተሰማርተው እያሉ፣ አንደኛው ላይ ከእነ ልብሱ ፖሊሱን
በማነቁ፣ ሌላኛው ላይ ደግሞ መሣሪያ ጭምር ለመቀማት እና የመተናነቅ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል ብለዋል።
በዚህም የተነሣ ፖሊሶቹ ነገሩን ለማብረድ ጥይት ተተኩሰዋል፣ድብደባም ተፈጽሟል በማለት ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።
የተፈጠረውን ድርጊት ተከትሎ የፖሊስ አባላቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ማጣራት እያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። ሆኖም ለድርጊቱ የአ.አ. ፖሊስ ኮሚሽን ኅብረተሰቡን ይቅርታ ይጠይቃል ብለዋል።
በድርጊቱ ላይ ተሳትፎ የነበራቸው ሁለት ፖሊሶች መታሰራቸውን፣ ጉዳዩን ለማወቅም በአካባቢው ገለልተኛ የሆኑ ሰዎችን የመጠየቅ፣ እውነተኛ ነገሩ መነሻው ምንድነው፣ የሚባለው ነው ወይስ ከዚያ ውጭ ነው የሚለውን ለማጣራት ኮሚሽኑ
ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑንም ኮሚሽኑ ለኢቲቪ ገልጿል።
ሆኖም ድርጊቱ ውስጥ የተሳተፉት የፖሊስ አባላት አዲስ እንደሆኑ እና ምንም ዓይነት የሥልጠና ጉድለት እንደሌለባቸው ያስታወቀው ኮሚሽኑ ፣ ኅብረተሰቡ የራሱ ልጆች መሆናቸውን በመረዳት፣ እነርሱ በሚሰጡት ዳኝነት ካልረካ ቅርብ ያለው አመራር ላይ ሔዶ ዳኝነት ለመውሰድ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ እንደሚገባም መክሯል።
በመጨረሻም ኅብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን ካልቆመ በስተቀር በተወሰነ የፖሊስ ኃይል ብቻ የወንጀል መከላከል ሥራ እንደማይሠራ በመረዳት ጥፋተኛ ፖሊሶቹን በማጋለጥ እና ሕግ ፊት እንዲጠየቁ በማድረግ እንዲሁም ስህተታቸውን ብቻ ሳይሆን ጥሩ ሥራቸውንም በጎላ መልኩ በማቅረብ ሊያበረታታቸው እና ወንጀልን በጋራ መከላከል ላይ ሊሳተፍ እንደሚገባ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽን እና የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለኢቲቪ ተናግረዋል።
@ETV

Sunday, 25 August 2019
Wednesday, 21 August 2019
Monday, 12 August 2019
Saturday, 10 August 2019
Thursday, 1 August 2019
ጠ/ሚሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ካነሷቸው ነጥቦች መሀል:
- ስለ ጄነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ: ወታደሩ
(ጠባቂው) አሁን በህክምና ላይ ይገኛል፣ አንገቱ
ላይ ቆስሏል። ከሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው
ተይዘዋል። ጥቃቱ የተፈፀመ ቅፅበት "(ጥቃቱ ሲፈፀም) ደውለህ ትነግረኛለህ" ብሎ ነገሮት በሁዋላ ደውሎ የነገረው ተይዟል።
- የሰኔ 15ቱን ሁኔታ አቅልሎ ማየት ልክ አይደለም። እንቅስቃሴ ሲደረግ የነበረው ተጨማሪ ጀነራሎችን ጭምር ለመግደል እንደነበር መረጃ ደርሶናል።
- እኔ በፊት የተለየ የህዝብ ተቀባይነት የነበረኝ፣ አሁን ደሞ የተለየ ተቀባይነት የሌለኝ ነበርኩ ብዬ አላስብም። ተቀባይነቱ ቀነሰ የሚሉ ምን መረጃ ኖሯቸው እንደሆነ አላውቅም።
- የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ገንዘብ አሰባሰብ እኔን ከመደገፍ እና ካለመደገፍ ጋር መያያዝ የለበትም። ሆኖም ከነበረ መሆን አልነበረበትም።
- በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ: አሁን ጭለማ ቤት ታስሮ ያለ የለም፣ ሰው አይገረፍም፣ ጥፍር አይነቀልም።
-ምርጫ: በኢህአዴግ ዘንድ ምርጫው አይደረግ የሚል አንድምታ የለም። ምርጫው ይካሄዳል ብለን እየተዘጋጀን ነው።
- ኢንተርኔት መዘጋት: መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ሊዘጋ ይችላል።

Subscribe to:
Posts (Atom)
Biruh Media
በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና
Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...