Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Thursday 1 August 2019

ጠ/ሚሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ካነሷቸው ነጥቦች መሀል:

- ስለ ጄነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ: ወታደሩ
 (ጠባቂው) አሁን በህክምና ላይ ይገኛል፣ አንገቱ
 ላይ ቆስሏል። ከሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው
 ተይዘዋል። ጥቃቱ የተፈፀመ ቅፅበት "(ጥቃቱ ሲፈፀም) ደውለህ ትነግረኛለህ" ብሎ ነገሮት በሁዋላ ደውሎ የነገረው ተይዟል።

- የሰኔ 15ቱን ሁኔታ አቅልሎ ማየት ልክ አይደለም። እንቅስቃሴ ሲደረግ የነበረው ተጨማሪ ጀነራሎችን ጭምር ለመግደል እንደነበር መረጃ ደርሶናል።

- እኔ በፊት የተለየ የህዝብ ተቀባይነት የነበረኝ፣ አሁን ደሞ የተለየ ተቀባይነት የሌለኝ ነበርኩ ብዬ አላስብም። ተቀባይነቱ ቀነሰ የሚሉ ምን መረጃ ኖሯቸው እንደሆነ አላውቅም።

- የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ገንዘብ አሰባሰብ እኔን ከመደገፍ እና ካለመደገፍ ጋር መያያዝ የለበትም። ሆኖም ከነበረ መሆን አልነበረበትም።

- በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ: አሁን ጭለማ ቤት ታስሮ ያለ የለም፣ ሰው አይገረፍም፣ ጥፍር አይነቀልም።

-ምርጫ: በኢህአዴግ ዘንድ ምርጫው አይደረግ የሚል አንድምታ የለም። ምርጫው ይካሄዳል ብለን እየተዘጋጀን ነው።

- ኢንተርኔት መዘጋት: መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ሊዘጋ ይችላል።

No comments:

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...