Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ - በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ነገ ይመረቃል ።
ፋብሪካዉ በቀን 1ሺህ 500 ቶን የምግብ ዘይት የሚያመርት ሲሆን፣ ለዘይት ይወጣ ከነበረው 30 በመቶ ወጪውን የሚያስቀር ነዉም ተብሏል ። ባለሃብቱና የቢኬጂ ቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ክንዴ በሰጡት መግለጫ ፍብሪካው ከዘይት ማምረት በተጨማሪ በቀን 200 ቶን ሰሊጥ ማቀነባበር : በቀን 96 ቶን ሳሙና ፣ የአትክልትና ማርጋሪት ማምረቻ፣ የፕላስቲክና ጠርሙስ እንዲሁም የካርቶን ፍብሪካዎችን በውስጡ እንደሚያመርት ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment