Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Saturday 6 February 2021

የኢትጵያ ንግደ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ አገኘ፡፡

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ -  የኢትጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2020 በጀት አመት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ 100 ባንኮች መካከል የ 17ኛ፣ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ 1ኛ ደረጃ በመያዝ አመቱን ማጠናቀቁን አፍሪካ ቢዝነስ እና ዘ አፍሪካ ሪፖርት በጥናታቸው ይፋ አደረጉ፡፡
የአፍሪካ ባንኮች በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በተከሰተው የኢኮኖሚና የንግድ መቀዛቀዝ ሳይበገሩ ከባለፉት 10 ዓመታት የተሻለ የካፒታል መጠን በማስመዝገብ አመቱን አጠናቀዋል፡፡ ባንኮች አማራጭ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች አማካኝነት ተደራሽነትን ለማስፋት ያደረጉት ጥረት የኮቪድ ተጽዕኖን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳስቻላቸው የጥናት ሪፖርቶቹ አስነብበዋል፡፡ 
 
 
 May be an image of skyscraper, sky and text
 
ጥናቶቹ እንዳመለከቱት አፍሪካ ውስጥ የባንኮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም፣ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር እና በባንክ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 ዓ.ም በናይጄሪያ 89 ባንኮች በአገልግሎ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ 2019 ዓ.ም የባንኮቹ ቁጥር ወደ 27 መውረዱ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ በኬንያም በተመሳሳይ 10 ባንኮች ሲዋሃዱ 3 ባንኮች ደግሞ ከስራ ውጭ ሆነዋል፡፡
በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ የሚንቀሳቀሰውና ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ላይ የተሰማራው ታይም ባንክ እ.ኤ.አ በየካቲት 2019 ዓ.ም በቀን እስከ 6000 የባንክ ሂሳቦች መክፈት የቻለ ሲሆን፣ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት እንቅስቃሴዎች በተገቱበት ወቅት ብቻ ከ400 ሺ በላይ የባንክ ሂሳቦችን በመክፈት ከ613 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል፡፡ ይህም በአፍሪካ ብዙ ያልተነካውን የዲጂታል የባንክ አገልግሎት በመጠቀም ባንኮቹ ወረርሽኙ የደቀነውን አደጋ መቋቋም መቻላቸውንና በገንዘብ ንክኪ ምክንያት ለወረርሽኝ መስፋፋት አመቺ የነበረውን አሰራር ማስቀረት መቻሉን አመላካች ነው፡፡

No comments:

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...