Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Sunday, 12 May 2024

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የጥበብ መዳረሻ ሆቴል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

ግንቦት 04 ቀን 2016(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለጥበብ ስራው መቃናት እና የጥበብ ባለሙያዎች መስራት በፈለጉት ሰዓት ስራቸውን ለመስራት እንዲረዳቸው ለማድረግ የሚያስችል የጥበብ መዳረሻ ሆቴል ሊገነባ መሆኑን የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
መዳረሻቸዉን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉ የበርካታ የዓለም ሃገራት ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በተለይም የጥበብ ሰዎች ለጉብኝት በመጡበት ወቅት የጥበብ ስራቸዉን እዚህ አከናዉነዉ መሄድ ቢፈልጉ ምቹ ቦታዎችን ማግኘት አዳጋች ይሆንባቸዋል፡፡
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 የ100ኛ አመቱን ክብረ በዓል ሲያከብር ሊያሳካቸዉና በሜጋ ፕሮጀክትነት ከያዛቸዉ እቅዶች መካከል የአርት ሪዚደንስ ወይም የጥበብ ስራዎችን ማከናወኛ ማዕከል የመገንባት ነዉ፡፡


የውጭ ዜጎች ለጉብኝት እና ለጥበብ ስራቸው ሲመጡ በማንኛው ሰዓት በሆቴሉ ተገኝተው ከእረፍታቸው ጎን ለጎን ስራቸውን ማስኬድ የሚችሉበት የጥበብ መዳረሻ ሆቴል አንድ ክፍለ ዘመን ለማስቆጠር በመንደርደር ላይ ባለው እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደሚገነባ የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ተናግረዋል፡፡
የጥበብ መዳረሻ ሆቴል በአፍሪካ በሰባት ሃገራት ውስጥ ብቻ እንዳለ የሚናገሩት አቶ ተሾመ፤ ባለሙያዎቹ መስራት በሚፈልጉበት ልክ በነፃነት እንዲሰሩ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነ እና ሙያውን ለማዘመንም እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡
መዲናችን አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ፤ ያሉት ሆቴሎች ለጥበብ ባለሙያዎች ምቹ እንዳልሆኑና እንዲህ አይነት ሆቴል መኖሩ ደግሞ በርካታ ቱሪስቶችን ለመሳብ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

No comments:

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...