Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Thursday 25 July 2019

ችሎቱ



በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን የአቶ በረከት ስምዖን፤ የአቶ ታደሰ ካሳን እና በአባሪ ተባባሪነት የተጠረጠሩትን የቀድሞ የብአዴን-ኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጉዳይ የሚዳኘዉ ፍርድ ቤት፣ አቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ ያቀረባቸዉን የሰነድ ማስረጃዎች በአማርኛ ቋንቋ ተርጎሞ እንዲያቀርብ አዘዘ።


ዛሬ ባሕርዳር ያስቻለዉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዳለዉ አቃቤ ሕግ ካቀረበዉ ከ1000 ገፅ የሚበልጥ የሰነድ ማስረጃ መካከል አብዛኛዉ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተፃፈ ነዉ። የክልሉ የሥራ ቋንቋ አማርኛ በመሆኑ አቃቤ ሕግ ለምስክርነት ያቀረበዉን ሰነድ ሙሉ በሙሉ በአማርኛ አስተርጎሞ ለመስከረም 22፣ 2012 እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ አዝዟል። ተከሳሾች ደግሞ መስከረም 30፣ 2012 እንዲቀርቡ ወስኗል። ተከሳሾች ግን፣ አቃቤ ሕግ ሰነዶቹን ሳይተረጉም ያቀረበዉ «ሆን ብሎ» ክሱ የሚታይበትን ጊዜ ለማራዘም ነዉ በማለት ቅሬታቸዉን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል። የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን እንደጠቀሰዉ አቃቤ ሕግ ማስረጃዎቹን እስካሁን በነበረዉ ጊዜ አስተርጎሞ ማቅረብ ይገባዉ እንደነበር ለችሎ
ቱ አስተያየት ሰጥተዋል።

No comments:

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...