Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Thursday 19 September 2019

በክብር እንግድነት እንዲገኙልን ስለመጋበዝ

ቁጥር፡MHEMD/03/001/12
ቀን፡ 08/01/12 ዓ.ም.

ለ_________________________

ጉዳዩ፡- በክብር እንግድነት እንዲገኙልን ስለመጋበዝ
መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን በተለይም ደግሞ እራሳቸውን ችለው መፀዳዳት፣ መመገብና መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑና የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን 2,000 በላይ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን ከወደቁበት ጎዳና በማንሳት አያት ኮንዶሚንየም አጠገብ በሚገኘው የመቄዶንያ ግቢ ውስጥ አመቺ መጠለያ በማዘጋጀት የምግብ፣ አልባሳት፣ ህክምናና ተገቢውን እንክብካቤና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ 
ማዕከሉ የበጎ አድራጎት ስራውን ለማስፋፋት ከ1.2 ቢልዮን ብር በላይ የሚፈጅ 2B+G+11 ህንፃ ግንባታ መጀመሩ፣ በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞችና እና በሁሉም ክልል ከተሞች በጎ ስራውን በማስፋፋት  የተረጅዎችን ቁጥር ወደ 10 ሺህ ለማሳደግ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
 በመሆኑም ለዚሁ በጎ ተግባር ከጎን የነበሩትን ሁሉ ለማመስገንና የዶክተር ብንያም በለጠን የሽኝት ዝግጅት ለማድረግ የምስጋና ዝግጅት የፊታችን እሁድ ሴፕቴምበር 22 ፤ ከሰዓት በ5 pm አለም ገበያ 640 S Pickett St, Alexandria, VA 22304 ላይ የምናካሂድ ሲሆን በክብር እንግድነት ተገኝተው ዝግጅቱን አብረውን እንዲያሳልፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
ከምስጋና ጋር

መርዳት ለምትፈልጉ

GoFundMe/ Mekedonia

የባንክ ሂሳብ ቁጥር

MEKEDONIA CHARITY HOMES
Bank Acc. Information: Wells Fargo Bank Acct.No: 6089212333 (Checking Account)                                                  Contact Phone No. 301-814-4883/ 202-352-6503
E-mail:binbenj@aol.com/mekedoniaelders@gmail.com

ቁጥር፡MHEMD/03/002/12
ቀን፡ 08/01/12 ዓ.ም.

ለ_________________________

ጉዳዩ፡- በእንግድነት እንዲገኙልን ስለመጋበዝ
መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን በተለይም ደግሞ እራሳቸውን ችለው መፀዳዳት፣ መመገብና መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑና የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን 2,000 በላይ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን ከወደቁበት ጎዳና በማንሳት አያት ኮንዶሚንየም አጠገብ በሚገኘው የመቄዶንያ ግቢ ውስጥ አመቺ መጠለያ በማዘጋጀት የምግብ፣ አልባሳት፣ ህክምናና ተገቢውን እንክብካቤና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ 
ማዕከሉ የበጎ አድራጎት ስራውን ለማስፋፋት ከ1.2 ቢልዮን ብር በላይ የሚፈጅ 2B+G+11 ህንፃ ግንባታ መጀመሩ፣ በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞችና እና በሁሉም ክልል ከተሞች በጎ ስራውን በማስፋፋት  የተረጅዎችን ቁጥር ወደ 10 ሺህ ለማሳደግ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
 በመሆኑም ለዚሁ በጎ ተግባር ከጎን የነበሩትን ሁሉ ለማመስገንና የዶክተር ብንያም በለጠን የሽኝት ዝግጅት ለማድረግ የምስጋና ዝግጅት የፊታችን እሁድ ሴፕቴምበር 22 ፤ ከሰዓት በ5 pm አለም ገበያ 640 S Pickett St, Alexandria, VA 22304 ላይ የምናካሂድ ሲሆን በእንግድነት ተገኝተው ዝግጅቱን አብረውን እንዲያሳልፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
ከምስጋና ጋር

መርዳት ለምትፈልጉ

GoFundMe/ Mekedonia

የባንክ ሂሳብ ቁጥር

MEKEDONIA CHARITY HOMES
Bank Acc. Information: Wells Fargo Bank Acct.No: 6089212333 (Checking Account)                                                  Contact Phone No. 301-814-4883/ 202-352-6503
E-mail:binbenj@aol.com/mekedoniaelders@gmail.com

Monday 16 September 2019

የ“ጊፋታ አዋርድ” ሽልማት ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሰጠ



የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ “ ጊፋታ አዋርድ” የተሰኘ የምስጋናና የዕዉቅና ሽልማት ተበረከቶላቸዋል::

በወላይታ ሶዶ “አርአያዎቻችን በረከቶቻችን ናቸው” በሚል መርህ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋናና ዕውቅና ስነ-ስርዓት ሲካሄድ

በስነ-ስርዓቱ ወቅት አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ በተለዩ አምስት ዘርፎች በሃገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጎ ተጽዕኖ የፈጠሩ 45 ግለሰቦች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል፡፡
በፖለቲካ፣ በንግድና ቢዚነስ፣ በኪነ-ጥበብ ፣በትምህርት ፣ባህልና ኃይማኖትና ህክምናው ዘርፎች ከአካባቢ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ በጎ አስተዋጽኦ የነበራቸው 45 ግለሰቦች ለመጀመሪያ ዙር እንዲታወሱና እንዲመሰገኑ ሽልማቱ እንደተሰጣቸው ተደርጓዋል፡፡

በኃይማኖቱ እነ አቡነ ተክለ-ኃይማኖትና አባባ ዋንዳሮን ጨምሮ በህይወት የሌሉ ነገር ግን አከባቢውን በበጎ መልኩ ያስተዋወቁ ሽልማቱና ዕውቅናዉ ከተበረከተላቸው መካከል ተጠቅሰዋል፡፡

በፖለቲካ አመራርና በትምህርት በሌሎች ጉዳዮች እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማበረከቱት አስተዋጽኦ ሽልማቱ የተበረከተላቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና ባለቤታቸዉ ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ናቸው፡፡

ለአቶ ኃይለማሪያ በአካባቢው ባህል መሰረት በፖለቲካው የአመራር ብስለትና ክህሎት በቀጣይም ከአብራኩ መሪ አይጥፋ በሚል የሚሰጥ ጦር፣ጋሻና የፈረስ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨረሲቲ እንዲመሰረት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በእጅ ጥልፍ የተሰራ ምስል ተሸልመዋል።

አቶ ኃይለማሪያም ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ የተዘጋጀው ስነስርዓት በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥና የአንድነት ጉዞ ለማጠናከር የጎላ አስተዋጽኦ አንደሚኖረዉ ተናግረዋል።

“ጊዜው የይቅርታ ነው” ያሉት አቶ ኃይለማሪያም በነበራቸው የስልጣን ቆይታ ወቅት የተፈጠሩ ስህተቶችን ህዝቡ ይቅር እንዲላቸው በመጠየቅ በቀጣይም ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ኢዜአ

Tuesday 10 September 2019

ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ ውዝግብ አስነሳ


በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ነው፡፡
ባለቤትነቱ የአቶ ደነቀ ሸለመ የሆነው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ ገዢዎችን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የወይዘሮ ሃጫልቱ በድሩን 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ላይ አነጣጥሮ ከጆሮዋ ላይ በጥሶ ይውጣል።

 ነገሩ ከተከሰተ በኋላ የዶሮው ባለቤትና የወርቋ ባለቤት ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባሉ፡፡

No photo description available.


የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው ወዲያው ታርዶ ወርቃቸው እንዲሰጣቸው ቢሹም የዶሮው ባለቤት ደግሞ በጉዳዩ አልተስማሙም።
ነገሩ መክረሩን ያዩት ገቢያተኞች ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ በማድረግ በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡


ጉዳዩ እንግዳ የሆነበት የወሊሶ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ጣቢያም ጉዳያቸውን በመስማማት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል።

የዶሮው ባላቤትም ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው የሚያወጣውን ዋጋ ከፍለው ዶሮውን ይረከቡኝ ሲሉ ይስማማሉ።


አቶ ደነቅም የወርቁ ባለቤት 250 ብር እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ባለ ወርቋ የተጠየቀውን ብር የለኝም በማለታቸው 150 ብር ሰጥተዋቸው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ነው የወሊሶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ

የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ከበደ በዳዳን ጠቅሶ ኢዜአ የዘገበው።
@ ኢዜአ

Sunday 8 September 2019

Ethiopia : የመጋቢ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ አስደናቂ ኢትዮጵያዊ ኩራት እና የስነፈለግ ምርምር ትንተና |Megabe Haddis Rodas Tadese


via IFTTT

Ethiopia : የመጋቢ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ አስደናቂ ኢትዮጵያዊ ኩራት እና የስነፈለግ ምርምር ትንተና |Megabe Haddis Rodas Tadese


via https://youtu.be/5pycKz4YVv8

Ethiopia :Tewolde GebreMariam CEO Ethiopian Airlines speech |


via IFTTT

Ethiopia :Tewolde GebreMariam CEO Ethiopian Airlines speech |


via https://youtu.be/pDx5Z8ENCu4

Ethiopia : New Music clip Making 2019 | በአዲስ አበባ ቸርችል አካባቢ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ ቀረፃ


via https://youtu.be/FMWhRtFsn-M

Ethiopia : New Music clip Making 2019 | በአዲስ አበባ ቸርችል አካባቢ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ ቀረፃ


via IFTTT

Ethiopia : New Music clip Making 2019 | በአዲስ አበባ ቸርችል አካባቢ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ...

Monday 2 September 2019

ዳቦ ቤቶች በህገወጥ መንገድ መሸጥ መድረሳቸው



ዳቦ ቤቶች የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በህገወጥ መንገድ እስከ መሸጥ መድረሳቸው ተነገረ    በመድረኩ ለውይይት በወቀረበው ሰነድ ላይ እንደተገለፀው መንግስት ለህዝብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ሲል የአንድ ዳቦ ዋጋ በ1 ብር 30 ሳንቲም ተምኖ ለዚህ የሚውል ስንዴን በድጎማ በ550 ብር እያቀረበ ይገኛል፡፡

 https://cdn.imgbin.com/5/13/9/imgbin-bakery-panini-small-bread-basket-bread-material-free-to-pull-bread-on-basket-illustration-ctPny1PmjX9pmuLGcVWighSVN.jpg

ሆኖም ዳቦ ቤቶች ስንዴውን ገበያ በማውጣትና ‘ልዩ ስንዴ’ በማለት በ2 ሺህ ብር እየሸጡ 1 ብር 30 ሳንቲም የነበረ የዳቦ ዋጋ 3 ብር ድረስ ሲሸጥ እንደተደረሰበት በሰነዱ ላይ ቀርቧል፡፡
ከዚህ ባለፈ ዳቦ ቤቶች የተፈቀደላቸው ዳቦ እንዲያቀርቡ ቢሆንም ኩኪስ፣ዶናት፣ ኬክና መሰል ምርቶችን በድጎማው ስንዴ አምርተው በመሸጥ ላይ እንደሚገኙም በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረት ቁጥጥር ሲደረግ በተቀመጠላቸው ዋጋ መሰረት ሲሰሩ የነበሩ ዳቦ ቤቶች አርበኞች፤ ሮዛ፤አፍሪካ እና ምስራቅ ዳቦ ቤቶች ብቻ መሆናቸውም ተያይዞ ተገልጿል፡፡

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...