Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Sunday, 12 May 2024

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የአየር ትንቢያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ በተገለፀው መሠረት የ2016 ዓ ም በልግ ዝናብ በተለያዩ አከባቢዎች ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል።
Uploading: 983724 of 983724 bytes uploaded.


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ ተከትሎ 148 ቀበሌዎች ከ75 ሺህ በላይ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ለጎርፍና ለአፈር ናዳ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸው የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ።
መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ የበልግ ዝናብ ስርጭት በክልሉ የጎርፍና የአፈር ናዳ አደጋዎችን ሊያስከትል ይችላል። በተለይ ጎፋ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ አሌ እና አሪ ዞኖች ለጎርፍና ለናዳ እንዲሁም ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶና ጌዴኦ ዞኖች ለጎርፍ አደጋ የመጋላጥ ስጋት ያለባቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የጥበብ መዳረሻ ሆቴል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

ግንቦት 04 ቀን 2016(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለጥበብ ስራው መቃናት እና የጥበብ ባለሙያዎች መስራት በፈለጉት ሰዓት ስራቸውን ለመስራት እንዲረዳቸው ለማድረግ የሚያስችል የጥበብ መዳረሻ ሆቴል ሊገነባ መሆኑን የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
መዳረሻቸዉን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉ የበርካታ የዓለም ሃገራት ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በተለይም የጥበብ ሰዎች ለጉብኝት በመጡበት ወቅት የጥበብ ስራቸዉን እዚህ አከናዉነዉ መሄድ ቢፈልጉ ምቹ ቦታዎችን ማግኘት አዳጋች ይሆንባቸዋል፡፡
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 የ100ኛ አመቱን ክብረ በዓል ሲያከብር ሊያሳካቸዉና በሜጋ ፕሮጀክትነት ከያዛቸዉ እቅዶች መካከል የአርት ሪዚደንስ ወይም የጥበብ ስራዎችን ማከናወኛ ማዕከል የመገንባት ነዉ፡፡


የውጭ ዜጎች ለጉብኝት እና ለጥበብ ስራቸው ሲመጡ በማንኛው ሰዓት በሆቴሉ ተገኝተው ከእረፍታቸው ጎን ለጎን ስራቸውን ማስኬድ የሚችሉበት የጥበብ መዳረሻ ሆቴል አንድ ክፍለ ዘመን ለማስቆጠር በመንደርደር ላይ ባለው እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደሚገነባ የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ተናግረዋል፡፡
የጥበብ መዳረሻ ሆቴል በአፍሪካ በሰባት ሃገራት ውስጥ ብቻ እንዳለ የሚናገሩት አቶ ተሾመ፤ ባለሙያዎቹ መስራት በሚፈልጉበት ልክ በነፃነት እንዲሰሩ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነ እና ሙያውን ለማዘመንም እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡
መዲናችን አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ፤ ያሉት ሆቴሎች ለጥበብ ባለሙያዎች ምቹ እንዳልሆኑና እንዲህ አይነት ሆቴል መኖሩ ደግሞ በርካታ ቱሪስቶችን ለመሳብ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን : የአለም አቀፉ የሮቦ ፌስት ውድድር አሸናፊ ሆኑ

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ


#Ethiopia | ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ህፃናት በአሜሪካ በተካሄደው የአለም አቀፍ የሮቦ ፌስት ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ሶስት ሽልማቶችን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን÷ የመጀመሪያው ከ 10 አመት በታች በተወዳደሩበት ሮቦ ፓሬድ የውድድር ዘርፍ ነው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በሲንየር ኤግዚቢሽን ከ 14 እስከ 16 አመት ስፔሻል አዋርድ ሽልማትን ማግኘት ችለዋል፡፡


በጁንየር እግዚቢሽን ዘርፍ ደግሞ በአለም አቀፍ ዉድድር የሶስተኝነትን ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ሲሆን÷በተጨማሪም ከየውድድሩ ከ 1 እስከ 3 ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አሜሪካ በሚገኘው የሚችጋን ላውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ውድድር 23 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ወክለው በተለያዩ ዘርፎች ለውድድር መቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

‹‹ኑሮን ለማሸነፍ ብዙ ፈተና አልፌአለሁ›› ድምጻዊ ካሳሁን እሽቱ

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ




#Ethiopia | ከሰሞኑ "ይሁን" አዲስ የሙዚቃ አልበሙን ያስመረቀው ድምጻዊ ካሳሁን እሸቱ በደስታው ቀን መነጋገሪያ የሆነ አንድ ተግባር ፈጽሟል፡፡
የሥራ ባልደረቦቹና ወዳጆቹ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት ቅንጡ ሊሞዚን ተከራይተው አልበሙ ወደሚመረቅብት ሸራተን የእንሂድ ግብዛ ቢያቀርቡለትም እርሱ ግን የህዝብ አገልግሎት በሚሰጥ ሚኒባስ ታክሲ ረዳት ሆኖ ወደ ድግሱ ሥፍራ መሄድን መርጧል፡፡
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ለመሰንብቻ ፕሮግራም ስለሆነው እንዳለው ‹‹ሁላችንም መነሻችንን፣ ማንነታችንን እንዳንረሳ አስቤ ያደረግሁት ነው›› ብሏል::
ካሳሁን ሙዚቃ ከመጀመሩ በፊት የታክሲ ረዳት ሆኖ መስራቱንም አስታውሷል::
በዚሁ ተግባሩ የታክሲ ረዳት ሆኖ ታክሲው በሚሄድበት መንገድ የነበሩ ተሳፋሪዎችን እየጠራ ሄዷል፡፡


‹‹ኑሮን ለማሸነፍ ብዙ ፈተና አልፌአለሁ፤ ብዙ ዓይነት ሥራዎችን ሠርቻለሁ፤ ከሠራኋቸው ሥራዎች አንዱ ታክሲ ረዳትነት ነው›› ይላል፡፡
ይህን ለማስታወስ ያደረገው ተግባርም እንዳስደሰተው ለመሰንበቻ የሬድዮ ፕሮግራም ተናግሯል፡፡
ካሳሁን እሸቱ በቅርቡ "ይሁን" የተሰኝውን የመጀመሪያ አልበሙን ለአድማጭ ማውረቡ ያወቃል::
ደሳለኝ ስዩም

ታላቋ አርበኛ ወይዘሪት ሆይ ከበደች ስዩምን የሚዘክር መርሃ ግብር ነገ ይካሄዳል

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

አርበኛ ወይዘሪት ሆይ ከበደች ስዩምን የሚዘክር መርሃ ግብር በነገው ዕለት ቅዳሜ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽ ታላላቆች በታደሙበት ይከናወናል፡፡ በተጨማሪም የአርበኛዋን አንጸባራቂ ገድል የሚያሳይ  አጭር ድራማም ለታዳሚው ይቀርባል፡፡

በታሪካችን ሂደት ሴቶች  ያላቸውን አስተዋፅኦ የሚዘክር ልዩ የፓናል ውይይት ከኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ጋር ታጅቦ እንደሚቀርብም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ዶ/ር ዘካሪያስ አምደብርሀን፣ ሴቶችን ከኢትዮጵያ ታሪክ አንጻር የሚያስቃኝ ጥናታዊ ጽሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ወይዘሮ ዮዲት አምሀ አበራ ደግሞ  የሴቶችን የስነልቦና ጥንካሬና እንዴት ይበረታታሉ? በሚለው ላይ አተኩረው ጥናታዊ መረጃ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡




 የህግ ባለሙያዋ ወይዘሮ ማሪያ ሙኒር ደግሞ  ሴቶች ከወንድሞቻቸው ጎን በመቆም  እንዴት የለውጥ ሀዋርያ ይሆናሉ? በሚለው ላይ ሀሳብ ያጋራሉ፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ አመት ተማሪ  ኤልዳና ዮሀንስ በበኩሉ፤ አዲሱ ትውልድ ምን ይጠበቅበታል? በሚለው ላይ ጠንካራ ሀሳብ  እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡ 

በነገው ዕለት የሚታወሱትና የሚዘከሩት አርበኛ ወይዘሪት ሆይ  ከበደች ስዩም፤ የዛሬ 83 አመት በተደረገው የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት ላይ  ከፍተኛ የድል መንፈስ የነበራቸውና በጦር ሜዳው ላይም በጀግንነታቸው የተወደሱ ነበሩ፡፡

Saturday, 11 May 2024

"ማያዬ" የሙዚቃ አልበም

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

እጅግ ደስ ብሎኛል!
ወዳጆቼ ደስ ይበላችሁ!!
ማያዬ እኔ እናንተን ፤ እናንተ ደግሞ እኔን የምታዩበት ፤ የዐይን ብሌን ወይም አሻግሮ ማያ መነፅር ነው ።
በዘመናት የጥበብ ጉዞ የበርካታ ጠቢባን ውህደት ፤ ትጋት እና ትዕግስት ውጤት የሆነውን የበኩር የሙዚቃ አልበሜን ወደ እናንተ ለማድረስ ሽር ጉዴን ጨርሼ ፤ ቀን ቆርጫለሁ ።


“ማያዬ” የሙዚቃ አልበም በቀጣይ አርብ ፤ ማለትም ግንቦት 9 / 2016 ዓ.ም በናሆም ሬከርድስ በሁሉም ኦንላይን ፕላትፎርሞች ላይ ይለቀቃል።
በማያዬ የልቤን ፤ የልፋቴን ፤ በአጠቃላይ እኔነቴን እንድታዩልኝ ለዓመታት ስሰናዳበት የነበረውን የጥበብ እልፍኜን መግቢያ በር ገርበብ አድርጌ ከፍቼዋለሁ ።
ድጋፋችሁ ፤ ፍቅራችሁ ፤ ሀሳብ አስተያየታችሁ ከመቼውም ጊዜ በላይ ያስፈልገኛል።
በማያዬ ዕንድንተያይ ይሁን ። አሜን !

ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ የተመሰረተበትን የ50ኛ ዓመት ክብረ በዓል በይፋ ማክበር ጀመረ

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

  ባለፉት 50 ዓመታት ከ8ሚ. በላይ ዜጎችን መድረስ ችሏል

  በአሁኑ ወቅት 700ሺ ዜጎች የፕሮጀክቱ  ተጠቃሚዎች ናቸው

  ትልቅ የሀገር ሃብት ነውና መከበርና መጠበቅ አለበት ተብሏል


ላለፉት አምስት አሰርት ዓመታት የቤተሰባቸውን እንክብካቤ ያጡና የቤተሰባቸውን እንክብካቤ ለማጣት በአደጋ ላይ ያሉ ህፃናትን የቤተሰብ እንክብካቤና ጥበቃ አግኝተው እንዲያድጉ ለሁለንተናዊ ዕድገታቸው የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ በማሟላት እንክብካቤ በመስጠት የሚታወቀው ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ፤ የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በዓል  በይፋ ማከበር ጀመረ። 

ድርጅቱ በእነዚህ አመታት፤ በአማራጭ የቤተሰብ ክብካቤ፣ በቤተሰብና ማህበረሰብ አቅም ግንባታ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲሁም በትምህርት በጤናና በወጣቶች ማብቂያ ፕሮግራሞች ከ8ሚ. በላይ ዜጎችን መድረስ እንደቻለ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡  

ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ የተመሰረተበትን የ50ኛ ዓመት ክብረ-በዓል  አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ኤስ ኦ ኤስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዳይሬክተር አቶ ሳህለማርያም አበበ ክብረ-በዓሉን አስመልክተው ሲናገሩ፤ ”ለ50 ዓመታት በቁርጠኝነት ፣በፍቅርና በብዙ ለውጦች የታጀበውን ክብረ በዓል ለማክበር በመብቃታችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል።” ብለዋል፡፡

“ድርጅቱ ዛሬ የደረሰበት የስኬት ምዕራፍ የሰራተኞቻችን፣ የለጋሾቻችን፣ አጋሮቻችንና የምናገለግላቸው ማህበረሰቦች የጋራ ጥረትና የማያቋርጥ ድጋፍን የሚያንፀባርቅ ነው። በራስ መተማመንና በጥንካሬ የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች ሁሉ አልፈው የትናንት ህፃናት የዛሬዎቹን ብርቱ ወጣቶች ማሳያ ነው።” ሲሉም አክለዋል፡፡


ያለፉት ዓመታት የልማት ስራዎቹንና ስኬቶቹን ለመዘከር ዓመቱን ሙሉ የሚከወኑ የተለያዩ የድርጊት መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀቱን የገለፀው ኤስ ኦ ኤስ፤ ክብረ በዓሉ የድርጅቱን  ስኬቶችን ለማንፀባረቅ፣ ያበረከተውን  አስተዋፅኦ በጉልህ ለማሳየት፣ ድርጅቱን ያገለገሉትን ሰራተኞችና ደጋፊዎቹን ዕውቅና ለመስጠት እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙትን ህፃናት ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ዕድል እንደሚሰጠውም አመልክቷል። 

በ1966 ዓ.ም በአገራችን ለተከሰተው ድርቅ ከመንግስት ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ፣ የመጀመሪያ ሥራውን በመቀሌ የጀመረ ሲሆን፤ ዛሬ አገልግሎቱን አስፋፍቶ በ 9 ክልሎች ውስጥ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ፣ “ህፃናት በፍቅር በሰላምና በሙሉ ዋስትና ሲያድጉ ማየት” የሚል ራዕይ ያነገበ መሆኑን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፤ምንም እንኳን ዋና የትኩረት አቅጣጫዎቹ ህፃናት ቢሆኑም ቅሉ በአሁኑ ወቅት በማህበረሰብ ልማት ላይ በስፋት ተሰማርቶ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በአንድ የኢመርጀንሲ ፕሮጀክት ወደ ስራ የገባው ድርጅቱ፤ ዛሬ 41 ፕሮጀክቶች ላይ እየሰራ እንደሚገኝና ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ብቻ የህፃናት ፕሮጀክቶች እንደሆነ ይገልፃል። የኤስ ኦ ኤስ ዳይሬክተር እንዳስረዱት፤ የቀሩት የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች ናቸው።

ድርጅቱ በህፃናትና ቤተሰብ ላይ አተኩሮ ከሚያከናውናቸው ጉልህ ስራዎች ጎን ለጎንም፣ የወጣቶች ልማትና የስራ ፈጠራ፣ የአደጋ ጊዜ እርዳታ፣ የትምህርትና ጤና ስራዎችም ላይ በስፋት እንደሚሳተፍ ለማወቅ ተችሏል።

የኤስ ኦ ኤስ አመራሮች የ50ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን አስመልክተው በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር እንዲሁም ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተወክለው የተገኙ ሃላፊዎች ስለ ድርጅቱ በጎ ሥራዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

በአገሪቱ ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቷቸው ከሚንቀሳቀሱ 5ሺ የሚደርሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መካከል ኤስ ኦ ኤስ ተጠቃሽ ነው ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር ፤ድርጅቱ በስራውም በምግባሩም የተከበረና የተደነቀ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያው ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በግዙፍነቱ በአለማቀፍ ደረጃ የሚጠቀስ ነው ያሉት ም/ ዳይሬክተሩ፤ ትልቅ የአገር ሃብትና ተቋም በመሆኑ መከበርና መጠበቅ አለበት ብለዋል።

ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ1949 ጀምሮ የቤተሰብ እንክብካቤ ላጡ ህፃናት በፍቅር የተሞላ ቤተሰብ ሲሰጥ የቆየው የዓለማቀፉ የኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች ፌዴሬሽን አካል ነው። ኤስ ኦ ኤስ በመላው ዓለም በ132 አገራት የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዓለማቀፍ ደረጃ የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት እያከበረ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡


መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 የተመሰረተበትን 1ኛ ዓመት በዓል አከበረ

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

ግንቦት 01 ቀን 2016(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሃገሪቱ የሚዲያ ኢንዱስትሪ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በ2015 ዓ.ም በዲቢኤ ኮሙኒኬሽን ስር የተቋቋመው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጭ ማሕበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት የቻለው መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 የተመሰረተበትን የአንደኛ ዓመት በዓል በድምቀት አክብሯል ፡፡



ጣቢያው ከሬዲዮ በተጨማሪ በህትመት፤በቴሌቪዥን፤በዲጂታል ሚዲያና የስልጠና ማዕከል በማቋቋም የልዕቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በህትመትና በዲጂታል ሚዲያ ለአድማጮችና ተመልካቾች የተለያዩ መረጃዎችን እያቀረበ ይገኛል፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ ለጣቢያው ባልደረቦች፤ለተባባሪ አዘጋጆች እንዲሁም ለተለያዩ አጋር አካላት የእውቅና አሰጣጥ ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ለ18 ሰዓታት መደበኛ ስርጭቶች ሲኖሩት የቁምነገር፤የመዝናኛ የስፖርት ዜናና ፕሮግራሞቹን ለአድማጮች እያቀረበ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ሰዓታት ውስጥ በሳምንት ከ45 ሰዓታት በላይ በጣቢያው የውጪ ተባባሪ አዘጋጆች ተሸፍኗል።

Tuesday, 7 May 2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET154/07 May 2024 ጭስ አጋጠመው

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ 

ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET154/07 May 2024 ጭስ አጋጠመው። በረራው አዲስ አበባ ላይ አርፎ በተመደበው በር ተዘግቶ ተሳፋሪዎቹ በሰላም እንዲወርዱ ተደርጓል።
የጭሱ ክስተት መንስኤ በምርመራ ላይ ነው.




ይህ ለተከበራችሁ ተሳፋሪዎች ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን።
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የBiruh Media - ብሩህ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Biruh Media

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...