Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ
Wednesday, 17 February 2021
ታሪፍ ጭማሪ
Monday, 8 February 2021
Saturday, 6 February 2021
በቡሬ ከተማ የምግብ ዘይት ማምረቻ ተገነባ
Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ - በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ነገ ይመረቃል ።
ፋብሪካዉ በቀን 1ሺህ 500 ቶን የምግብ ዘይት የሚያመርት ሲሆን፣ ለዘይት ይወጣ ከነበረው 30 በመቶ ወጪውን የሚያስቀር ነዉም ተብሏል ። ባለሃብቱና የቢኬጂ ቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ክንዴ በሰጡት መግለጫ ፍብሪካው ከዘይት ማምረት በተጨማሪ በቀን 200 ቶን ሰሊጥ ማቀነባበር : በቀን 96 ቶን ሳሙና ፣ የአትክልትና ማርጋሪት ማምረቻ፣ የፕላስቲክና ጠርሙስ እንዲሁም የካርቶን ፍብሪካዎችን በውስጡ እንደሚያመርት ተናግረዋል።
የኢትጵያ ንግደ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ አገኘ፡፡
ዋሻ የከበሩ ድንጋዮች እና አርት ኢግዚቢሽን ተከፈተ።
Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ - ከዛሬ ጥር 29 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ለሁለት ቀናት መስቀል ፍላወር ዚግዛግ እና ስፖ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከፈተው ኢግቢሽን ላይ ሀያ አንድ ነጋዴዎች ተሳታፊዎች ናቸው። የሀገር ውስጥ ሸማቾችን ወደ ገበያው ለመሳብ አላማ ያደረገው ኢግዚቢሽን ላይ ስዕል፣የከበሩ ማዕድናት፣
የባህል አልባሳት፣የቆዳ ውጤቶች ፣የሀገር ውስጥ ማር፣ስእሎች፣የግእዝ የሰአትና የቀን አቆጣጠር ያላቸው ሰአቶችና ቀለበቶች እንዲሁም የተለያዩ ጌጣጌጦች፣የስጦታ ካርዶች እና ሌሎችም ቀርበውበታል።
Thursday, 4 February 2021
🔴 Ethiopia : የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በማህበራዊ ሚድያ ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ | Ethiopia
via https://youtu.be/Ak70n3tGf8I
የዶ/ር አምባቸው መኮንን ፋውንዴሽን ምስረታ ይፋ ሆነ
ፋውንዴሽኑ ዶክተር አምባቸው በህይወት እያሉ የጀመሯቸውን ሊሰሯቸው የሚችሏቸውን ስራዎች ለማስቀጠል እንደሆነ የዶክተር አምባቸው ልጅ መዓዛ አስታውቃለች።
ፋውንዴሽኑ በትምህርት፣ በጤና እና በአረንጓዴ ልማት ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ እውነትንና ሀቀኝነትን ይዞ የአገርን ልማት የሚያግዝ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።
ዳንኤል ክብረትን እናወግዛለን ማለትኮ
ብልፅግና ፓርቲን ለመደገፍ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ወዳጄ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሲወገዝ አይቸ ገረመኝ ! ብልጥግናን እንደግፋለን ዳንኤል ክብረትን እናወግዛለን ማለትኮ “ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እንሞታለን በረኛውን ግን እንገድለዋለን “ እንደማለት ነው
#DanielKibret #Ethiopia #biruhmedia#BewketuSeyoum
Wednesday, 3 February 2021
የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመሩ
Monday, 1 February 2021
ጀኔራል አበባዉ ታደሰ ህንፃዉን ተረከበ
የጀነራል አበባዉ ህንፃ የሆነዉ አልዋቅ ሆቴል በቀደሙት አመታት ለሼህ አላሙዲን ተሸጦ የነበረ ሲሆን መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ለባለቤቱ ጀነራል አበባዉ ተመላሽ ሆኗል ። ህንፃዉን ለባለቤቱ ተመላሽ እንዳደረጉ የገለፀዉ የመረጃ ምንጫችን ሼህ ሙሀመድ አላሙዲንም አልዋቅ ሆቴልን የራስህ ሆቴል ነበር አሁንም በትግስትህና ባለህ ቁርጠኝነትና ሀገርህ በምጥ ሰዓት ስትፈልግህ ለሂወትህ ሳትሰስት አለሁልሽ ብለህ ተገኝተሃልና ቀድሞውኑ ያንተ ነበር አሁንም በስምህ ይጽና የደምና የሂወት ዋጋህንም መልሰህ ውሰድ" በማለት ሆቴሉን መልሰው አስረክበውታል ሲል ጠቅሷል ።
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በምርጫ ዙሪያ ምላሽ ሊሰጡ ነዉ
በምርጫ ብቻ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ምርጫ ቦርድን ይጠይቁ በሚል ርእስ የማህበራዊ ሚድያ ተሳትፎ መድረክ በኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ የተዘጋጀ ሲሆን የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሀሙስ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት 5 ሰአት ላይ በፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለጠያቂዎቻቸዉ ምላሽ እንደሚሰጡ ምርጫ ቦርዱ በፌስቡክ ገፁ ላይ አስታዉቋል ፡ ማንኛዉም ሰዉ በዚህ የቀጥታ ስርጭት ላይም እንዲይሳተፉ፣ ጥያቄዎቻቸውንም በማህበራዊ ገፁ መልዕክት መሰጫ ላይ ቢልኩለት ዝግጁ መሆኑን አስታዉቋል ።
የምርጫ ቦርዱን ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ለማግኘት
በኢትዮጵያ የግንባታ ስራዎች ባልተገባ መንገድ በተወሰኑ ስራ ተቋራጮች እጅ እየገባ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር አስታወቀ።
በመሰረተ ልማት ስራዎች ዙሪያ እየተፈጠሩ ያሉ ተግዳሮቶች በተገቢው ሁኔታ ስራ መስራት እንዳልችል አድርጎኛል ሲል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር አስታወቀ፡፡ ማህበሩ በስራ ሂደት እየገጠሙኝ ነው ባላቸው የስራ መስኮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ማህበሩ በተለያዩ የግንባታ ዘርፎች መንግስታዊ ግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤቶች በኩል ከሚታዩ የኢፍትሃዊ የግንባታ ግዥ አፈጻጸም ጀምሮ እየተከናወኑ ያሉ ግንባታዎች በተወሰኑ ድርጅቶች ብቻ እንዲገነቡ የመፍቀድ ሁኔታዎች መበራከታቸው ግንባታዎችን ከማጓተቱ ባለፈ ለተለያዩ ብልሹ አሰራሮች እንዲጋለጥ እንዳደረገው ማህበሩ አስታውቋል፡፡
ሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች
ዛሬም በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል።
Biruh Media
በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና
Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝና ከባድ ብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረ...